ማንኛዉም የምግብ ምርት በባለስልጣኑ ሳይመዘገብ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የተከለከለ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ማንኛውም የምግብ ምርት በባለስልጣኑ ሳይመዘገብ እና የገበያ ፊቃድ ሳያገኝ ለሽያጭ ማቅረብ፣ ማስተዋወቅ ወይም የምርት ይዘት፣ ዓይነትና ሂደት ለውጥ ማድረግ እንደማይቻል አስታወቀ፡፡
በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በፀደቀው የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 71/2/ መሠረት የምግብ ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 42/2011 መውጣቱን በመግለጽ ማንኛውም የምግብ አስመጪ እና አምራች ቀድሞ Focal Person በማሳወቅ በመመሪያው የተቀመጡ መስፈርቶች /ሰነዶች/ን በማያያዝ በተቋሙ ድህረ ገጽ www.eris.efda.gov.et ላይ በOnline ምርቱን ማስመዝገብ እንድሚኖርበት ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳስቧል፡፡
ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን በማንኛውም ጊዜ ለሚደርሰዉ እንግልት እንዲሁም የዲሜሬጅ ኪሳራ ተቋሙ ተጠያቂ እንደማይሆን አስገንዝቧል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ ለህብረተሰቡ የሚቀርብ ማንኛውም የምግብ ምርት በባለስልጣኑ ሣይመዘገብ እና የገበያ ፊቃድ ሳያገኝ ለሽያጭ ማቅረብ፣ ማስተዋወቅ ወይም የምርት ይዘት፣ ዓይነትና ሂደት ለውጥ የተከለከለ መሆኑን አስታዉቋል፡፡