ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከመላ ሀገሪቱ ለተውጣጡ አንድ መቶ የምግብ ተቋማት ተቆጣሪዎች በምግብ ተቋማት የውስጥ ጥራት ማረጋገጥ፣ የምግብ ተቋማት የኦዲቲንግ ኢንስፔክሽን ቁጥጥር እና ሌሎች ዕርሰ ጉዳዮች ዙሪያ በአዳማ ከተማ በሄልዝ ኢንተርናሽናል ሆቴል የሚሰጠው ስልጠና የተጀመረ ሲሆን ስልጠናውም ከህዳር 5 እስከ 9/2011 ዓ.ም. ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ እንዳስታወቁት በምግብና መድኃኒት ጥራትና ደህንነት ላይ ብዙ የሚታዩ ችግሮች በመኖራቸው እንደአቅጣጫ ምርትን በመቆጣጠር ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ህበብረተሰቡን ከአደጋ ለመጠበቅ ባለስልጣን መስሪያቤቱ አራት ዋና ዋና ትኩረት የሚሰጣቸው የፍላግ ሺፕ ዕቅዶችን በማውጣት እነዚህም የህገወጥ ምግብና መድኃኒት ንግድ ይቁም፤ለመድኃኒት ምዝገባ ጥያቄ በአንድ ሳምንት ውስጥ ምላሽ መስጠት ፤ጥራቱን የጠበቀ መድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ለጤና አገልግሎት ጥራት ! እና ምግብን ከባዕድ ነገር ጋር መቀላቀል ይቁም! የሚሉ ናቸው፡፡
በማያይዝም በሀገር ደረጃ በወጣው የመቶ ቀን ሀገራዊ ዕቅድ የጤና ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው እና የህብረተሰቡ የጤና ስጋት የሆነው የምግብ ደህንነትና ጥራትን ማረጋገጥ ላይ አንደ ሚንስትር መስሪያቤቱ ቁጥጥሩን ማጠናከር ከፍተኛ ትኩረት ስጥቶ እየሰራ መሆኑንና ባለስልጣን መስሪያቤቱም እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ በመቀጠል በምግብና መድኃኒት ዙሪያ የተቀመጡትን የፍላግ ሺፕ ዕቅዶች ለማሳካት እና የኦዲቲንግ ኢንስፔክሽን ቁጥጥር በመላ ሀገሪቱ በወጥነት እንዲሰራ ስልጠናው እንደተዘጋጀ በመግልጽ ሰልጣነኞች ወደ የመጡበት ክልል ሲመለሱ ሁለት ሺ የአሰልጣኞች ስልጠና እንደሚሰጥ ሆኖ በምግብ ጋር በተያያዙ 113 ሺ የምግብ ተቋማት ላይ ቁጥጥር ስራዎች እንደሚሰራ ተገጿል፡፡
ስልጠናው ለቀጣይ አምስት ቀናት እንደሚቀጥል የታወቀ ሲሆን ሰልጣኞች ከሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች እና ከዘጠኝ ክልሎች እንደተውጣጡ ተገልጿል፡፡