የኮሮና ቫይረስ _ 19 በሽታ በቅርብ ጊዜ በተገኘ ኮሮና ቫይረስ ተብሎ በሚጠራ ቫይረስ ምክንያት የሚመጣ ተላላፊ በሽታነው። እስካሁን ድረስ ለዚህ በሽታ መከላከያ ክትባትም ሆነ መፈወሻ መድኃኒት የለውም፡፡ ሆኖም ተመራማሪዎች ለበሽታው መከላከያ የሚሆን ክትባትና መፈወሻ መድኃኒት ለማግኝት ሌት ከቀን እየሠሩ ሲሆን ውጤት ተገኝቶ አገልግሎት ላይ ለማዋል ብዙ ወራቶችን ስለሚጠይቅ አሁንም መንግሥትና የጤና ባለሙያዎች የሚነግሩንን ምክር ተቀብለን ተግባራዊ ማድረግ አማራጭ የሌለው አማራጭ ነው፡፡ የሚከተሉትን በጥንቃቄ በመፈጸም አዎ ይቻላል፡፡ 1) እጅን በውሀ እና በሳሙና ቶሎ ቶሎ በአግባቡ መታጠብ፣ ውሀና ሳሙና በአካባቢያችን ከሌለ ደግሞ የእጅ ማጽጃ ኬሚካሎችን (Hand sanitizer) በመጠቀም እጅን በደንብ ማጽዳት፤ 2) አለመጨባበጥ 3) አካላዊ ርቀትን መጠበቅ (ቢያንስ 2 የአዋቂ እርምጃ ወይንም 2 ሜትር ርቀት ጠብቀው መንቀሳቀስ) በአሁኑ ወቅት ከኮሮና ቫይረስ _ 19 በሽታ መከሰት ጋር ተያይዞ የተለያዩ ሀገራትና ብዙኃን መገናኛ የፊት መሸፈኛ ጭንብሎችን አስመልክቶ የተለያዩ መረጃዎችን እያወጡ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ተከትሎ በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ _ 19 በሽታ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ዜጎች የተለያዩ የፊት መሸፈኛ ጭንብሎችን ሲጠቀሙ ይታያል፡፡ ይሁን እንጂ ከበሽታው አደገኛነት ጋር ተያይዞ ስለምንጠቀምባቸው የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች ምንነት፣ ከምን እንደተሠሩ፣ የት እንደተሠሩ፣ አግባብ ያለው የመንግስት አካል ዕውቅና እንደሰጠው ማረጋገጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የፊት መሸፈኛ ጭንብል መጠቀም ብቻ በቫይረሱ ከመያዝም ሆነ ከማስተላለፍ ሙሉ በሙሉ ስለማይከላከል ሌሎቹን የመከላከያ መንገዶች ማለትም እጅን ቶሎ ቶሎ በአግባቡ መታጠብ፣ አልኮል ያለው ሳኒታይዘር መጠቀም፣ አካላዊ ርቀት መጠበቅና ባለመጨባበጥ መከላከል ይቻላል፡፡ የተለያዩ የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች በገበያ ላይ የሚገኙ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ _ 19 በሽታን የመከላከል አቅማቸው ግን በሚሠሩበት የጥሬ ዕቃ፣ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ይወሰናል፡፡ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎች ዓይነቶች፦ የእጅ ማጽጃ (Hand sanitizer) ማለት ተላላፊ የሆኑ በሽታ አምጪ ተሕዋስያንን ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን ከአልኮልና ከሌሎች ንጥረ ነገር በፈሳሽ ወይንም በቅባት መልክ የሚዘጋጅ ነው፡፡ ማንኛውም በሕጋዊ መንገድ የተመረተ ወይንም ወደ ሀገር ውስጥ የገባ የእጅ ማጽጃ (Hand sanitizer) የአልኮል መጠኑ ቢያንስ 80 በመቶ (80%) እና ከዚያ በላይ ከሆነ ተላላፊ የሆኑ በሽታ አምጪ ተሕዋስያንን የመከላከል አቅም ያለው ስለሆነ መጠቀም ይቻላል፡፡ የአመረተውን ድርጅት ስምና አድራሻ፣ የምርቱ መለያ ቁጥር ( batch number)፣ የአልኮል መጠኑ ከሰማኒያ በመቶ (80%) በታች አለመሆኑንና አገልግሎቱ የሚያበቃበት ወርና ዓመት መገለጻቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የኮሮና ቫይረስ _ 19 በሽታ በቅርብ ጊዜ በተገኘ ኮሮና ቫይረስ ተብሎ በሚጠራ ቫይረስ ምክንያት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው። የኮሮና ቫይረስ በሽታ አምጪ ተሕዋስያን በዓይን የማይታዩ በጣም ረቂቅ ስለሆኑ በቤት ውስጥ ከጨርቅ የሚዘጋጁ የፊት ጭንብሎች በበሽታው ከተያዘ ሰው የሚወጡ በቫይረሱ የተበከሉ የእርጥበት ቅንጣቶችን መከላከል እንደማያስችሉ የተለያዩ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሀገራት እነዚህን ከጨርቅ የተሠሩ የፊት ጭንብሎች በማህበረሰቡ ቢደረጉ የበሽታውን ሥርጭት ለመቀነስ ስለሚረዳ ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ሰዎች በሚበዙበት ቦታዎች ጭምብል ቢጠቀሙ ቫይረሱ እያለባቸው የህመም ምልክት ካልታየባቸው ወደ ጤናኛ የቫይረሱን መተላለፍ ሊቀንስ እንደሚችል ይጠቁማል፡፡ የሀገራችን የጤና ሚኒስቴርም ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች የፊት መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ እየመከረ ይገኛል፡፡ ለሕክምና አገልግሎት የሚውል የፊት መሸፈኛ ጭምብል (Medical mask) እና N95 የመተንፈሻ የሕክምና ጭንብል (Surgical N95 respirator) አምራቾችና አስመጪዎችን እውቅና እንዲሰጥ በሕግ ሥልጣን የተሰጠው ለኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ሲሆን ብቃታቸውን አረጋግጦ እንዲያመርቱ ወይንም እንዲያስመጡ ፈቃድ የሰጣቸውን ተቋማትና የምርቱን ስም ይህንን https://eris.efda.gov.et/public/temporary_coc በመጫን ይመልከቱ፡ የኮረና ቫይረስ በሽታ አምጪ ተሕዋስያን በዓይን የማይታዩ በጣም ረቂቅ ስለሆኑ በቤት ውስጥ ከጨርቅ የሚዘጋጁ የፊት ጭንብሎች በበሽታው ከተያዘ ሰው የሚወጡ በቫይረሱ የተበከሉ የእርጥበት ቅንጣቶችን መከላከል እንደማያስችሉ የተለያዩ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሀገራት እነዚህን ከጨርቅ የተሠሩ የፊት ጭንብሎች በማህበረሰቡ ቢደረጉ የበሽታውን ሥርጭት ለመቀነስ ስለሚረዳ ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች ጭንብል ቢጠቀሙ ቫይረሱ እያለባቸው የሕመም ምልክት ካልታየባቸው ወደ ጤናኛ የቫይረሱን መተላለፍ ሊቀንስ እንደሚችል ይጠቁማል፡፡ የሀገራችን የጤና ሚኒስቴርም ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች የፊት መሸፈኛ ጭንብል እንዲጠቀሙ እየመከረ ይገኛል፡፡ የእጅ ማጽጃ (Hand sanitizer) ማለት ተላላፊ የሆኑ በሽታ አምጪ ተሕዋስያንን ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን ከአልኮልና ከሌሎች ንጥረ ነገር በፈሳሽ ወይንም በቅባት መልክ የሚዘጋጅ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ከጨርቅ የተሠራ የፊት መሸፈኛ ጭንብል ለማምረት አምራቾችና አከፋፋዮች ሊከተሏቸው የሚገቧቸውን አሠራሮች በተመለከተ ያወጣውን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና የገበያ ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ይህንን http://www.fmhaca.gov.et/covid19-publications/ መጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡ እነዚህን ስልክ ቁጥሮች በመጠቀም 8482 ወይም +251-11-552-41-22 ወይንም በዚህ ኢሜል etcovid19@efda.gov.et መላክ ወይም ማሳወቅ ይችላሉ፡፡Load More
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19
Category: COVID-19