ትውልድን ከሱሰኝነት ለመታደግ ስለመንቀሳቀስ
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የመድኃኒቶችን ደህንነት፤ ፈዋሽነት፤ ጥራትና አግባባዊ አጠቃቀም ለማረጋገጥ የተሰጠውን ሕጋዊ ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት በርካታ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ በትራማዶል (Tramadol) መድኃኒት አግባባዊ አስተዛዘዝ፣ እደላ እንዲሁም አጠቃቀም ዙሪያ ጥናት ተደርጎ የነበረ ሲሆን የሚደርሱንም መረጃዎች የችግሩን አሳሳቢነት ያመላክታሉ፡፡ በዚሁ መሰረት አላግባብ የሆነ አጠቃቀም በጤና ተቋማት እና በመድኃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች መኖሩን አረጋግጠናል፡፡
ይህንን መድኃኒት አለአግባብበ መጠቀም የሚደርሰውን የጤና፣ የማህበራዊ፤ የኢኮኖማዊ እና የፖለቲካዊ አሉታዊ ተፅኖ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር አስፈላጊው እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በመሰራት ላይ ካሉ የቁጥጥር ስራዎች መካከል
- በመድኃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች እና በጤና ተቋማቶች ላይ ትራማዶል (Tramadol) ያለሀኪም ማዘዣ ለተጠቃሚ እንዳይደርስ ለሁሉም ክልል ተቆጣጣሪዎች ሰርኩላር ደብዳቤ ተጽፏል፡፡
- ትራማዶል ከፍተኛ ቁጥጥር ከሚደረግባቸው የናርኮቲክ መድኃኒት ዝርዝር ውስጥ ተካትቶ በድህረ-ገጽ እንዲታወቅ ተደርጓል::
- በጤና ተቋማት እና በመድኃኒት ችርቻሮ ድርጅቶች የክትትልና የቁጥጥር ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም እያንዳንዱ ሰው ትውልድን ለመታደግ እንዲረባረብ በባለስልጣኑ ስም ጥሪያችንን እያቀረብን ሕጉን ያላከበረ ተግባር ካስተዋሉ ለኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን በነፃ የስልክ መስመር 8482 ያሳውቁ፡፡