የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እና አመራሮች በያዝነው በጀት አመት የጤና ቁጥጥር ትኩረት አድርጎ የሚሰራባቸው /ፍላግ ሺፕሰ /እና የሩብ ዓመት እንቅስቃሴ ላይ ቀሊቲ በሚገኘው አዲስ በሚገነባው የጤና ቁጥጥር የልህቀት ማዕከል ግቢ ውስጥ ውይይት አደረጉ፡፡
የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ እንዳስታወቁት ባለስልጣን መስሪያቤቱ በያዝነው በጀት ዓመት በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ የገለፁ ሢሆን እነዚህም ህገወጥ ምግብና መድኃኒት ንግድ ይቁም!፤ለመድኃኒት ምዝገባ ጥያቄ በአንድ ሳምንት ውስጥ ምላሽ መስጠት!፤ጥራቱን የጠበቀ መድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያ ለጤና አገልግሎት ጥራት እንዲሁም ምግብን በባእድ ነገር መቀላቀል ይቁም! የሚሉት የፍላግሺፕ ዕቅዶች ላይ እየሰራ መሆኑን በመግለጽ ሁሉም ሰራተኛ ለእነዚህ እቅዶች መፈጸም አስተዋጾ ሰላለው በመረባረብ እና በመተባበር የጤና ቁጥጥር ዘርፉ ወደፊት ለማራመድ ጠንክሮ እንዲሰራ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በዕለቱ አዲስ የተሸሙት የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ከጠቅላለው የሰራተኛው ጋር ትውውቅ ያረጉ ሲሆን በንግገራቸውም እንዳሉት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ህዝብን ለማገልገል ከፍተኛ አላፊነት መሆኑን እና ለዚህም በታላቅ ትጋት ህዝቡን ለማገልገል ዝግጁነታቸውን በመግለጽ መለው ሰራተኛ ከጎናቸው በመሆን ለዕቅዱ መሳካት የበኩሉን አስተዋጾ እንዲያበረክት ጠይቀዋል፡፡
በሌላ በኩል ባለስልጣን መስሪያቤቱን ለአስር ተከታታ ዓመታታ በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት አቶ የሁሉ ደነቀው በክብር ተሸኝተዋል፡፡