ወ/ሪት ሄራን ገርባ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የ2015ዓ.ም የጤናው ዘርፍ የላቀ አመራር ተሽላሚ ሆኑ፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ የተሸለሙት በዛሬው ዕለት የ24ኛው የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ ሲጀመር ነው።
ወ/ሪት ሄራን ለሽልማት የበቁት የጤና ግብዓቶች ቁጥጥርን ውጤታማ በማድረግና ተቋሙን ወደ ተሻለ ደረጃ በማሽጋገር ላሳዩት የላቀ አመራር ነው።
ወ/ሪት ሄራን ሽልማቱን ሲቀበሉ ባደረጉት ንግግር ሽልማቱ የራሳቸው ብቻ ሳይሆን በየደረጃው የሚገኙ የባለስልጣኑ አመራርና ሠራተኞች ጭምር ነው ብለዋል።ሁሉንም የጤና ዘርፍ አካላት በማሳተፍ ጥቅምት 10 እና 11 2015 የሚቆየው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ “ፍትሐዊና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለሁሉም!” በሚል መሪቃል የ2ተኛ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የ2ተኛ ዓመት ግምገማ፣ የ2014 ዕቅድ አፈፃፀምና የ2015 መሪ ዕቅድ ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።