የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን/FDA ከዘጠኝ ክልሎችና ሁለት ከተማ መስተዳድር ከተወጣጡ የምግብ ተቋማት ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች የምግብ ደህንነትና ጥትራት ቁጥጥር ማረጋገጥ ሚያስችል የቁጥጥር አቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኝል፡፡
ባለስልጣን መስሪቤቱ እየተሰጡ ያሉት ስልጠና መሰረታዊ የቁጥጥር አሰራር ስርዓት፣ በምግብ ተቋማት የውስጥ ጥራት ማረጋገጥ፣ የምግብ ተቋማት የኦዲቲንግ ኢንስፔክሽን ቁጥጥር እና ሌሎች ዕርሰ ጉዳዮች ዙሪያ በአዳማ ከተማ ከህዳር 13 እስከ 17/2011 ዓ.ም. ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው ስልጠና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ከይረዲን ረዲ እንደገለጹት በስፋት በህብረተሰቡ ውስጥ እየታዩ ያሉ የጤና ችግሮች ከምግብ ደህንነት እና ጥራት ጋር ተያያዝነት ያሉ መሆኑን በማስታወቅ እነዚህም ጥራታቸው ያልተረጋገጡ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የጨቅላ ህጻናት ምግቦች፣ የታሸጉ ዱቄት ወተቶች ፣ብስኩቶች ፣ጁሶች እና በስፋት ህብረተሰቡ የሚጠቀምባቸው እንደ ዘይት ያሉ ምርቶችን እንደሚካትትት በመግለጽ ፤የተበላሹ የነቀዙ እና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ምግቦችን በህገወጥ መንገድ በማዘዋወር የህብረተሰቡን ጤና አደጋ ላይ የሚጥሉ ስራዎች በድብቅ የሚሰሩ አካላትን የተቀናጀና ወጥነት ያለው የቁጥጥር ስራ በመስራት ከምግብ ጋር ተያይዞ እየገጠሙ የሚገኙትን ችግሮችን መፈታት አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ምግብን ከባእድ ነገሮች ጋር በመደባለቅ የህብረተሰቡን ጤና አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ስራዎች እንደሚሰራ በማውሳት እነዚህን መሰል ተግባራት ለማስቆም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፌዴራል እስከ ክልል ፤ከክልል እስከ ወረዳ በቅንጅት መሰራት እንደሚያስፈልግ ገልጿል።
የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ለቁጥጥር ስራው ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ የገንዘብና የማቴሪያል ደጋፍ እየተደረገ ሲሆን በባለስልጣን መስሪያቤቱም የፍላግ ሺፕ ዕቅዶች ይሄም ምግብን ከባዕድ ነገር ጋር መቀላቀልንና የህገወጥ ምግብና መድኃኒት ንግድን ለማስቆም ለተቆጣጣሪው አቅም የመፍጠር ስራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የአሰልጣኞች ሰልጠና ከተጠናቀቀ ቦኃላ ከክልል እስከ ወረዳ ላሉ 2000 ተቶጣጣሪ ባለሙያዎች በክልል ተቶጣጣሪ አካላት ተመሳሳይ ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን 113 ሺ የምግብ ተቋማት ቀጥጥር እንደሚካሄድ ይጠበቃል።