የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በመግቢያና መዉጫ ኬላዎች ላይ በምግብና መድኃኒት ምርቶች ባደረገዉ የቁጥጥር ስራዎች የተመዘገቡ ዉጤቶችን ይፋ ተደረገ፡፡
በ23 የምግብ ዓይነቶች ላይ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ፤ በቁጥር ወደ 208 ናሙናዎች በዚህ ሶስት ወር የጥራት ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን 195 የምግብ ዓይነቶች መስፈርቱን ሟሟላት ሲችሉ 13 ናሙና የሀገሪቷን ደረጃ ባለሟሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ተደርጓል፡፡