የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አመራሮችና ሠራተኞች በቃሊቲና ሞጆ ከተማ ችግኝ ተከሉ፡፡
በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የተያዘውን የአረንጋዴ ልማት ፕሮግራም ለማሳካት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮች እና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ ቀንን በማስመልከት በአዲስ አባባ ከተማ በቃሊቲ እና በኦሮሚያ ክልል በሞጆ ሎሚ ወረዳ ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም በመገኘት በተዘጋጀላቸው ቦታ ችግኞችን ተክለዋል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት አመራረሮችና ሠራተኞች በሞጆና በቃሊቲ የችግኝ ተከላውን ያካሄዱ ሲሆን በተመሳሳይ በድሬዳዋ፣ በጅማ፣ በሐዋሳ፣ በኮንቦልቻና በባህር ዳር የሚገኙ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሠራተኞችም በተመረጡ ቦታዎች ላይ ችግኝ መትከላቸው ታውቋል፡፡
ከዚህ ቀደም የባለሥልጣን መሥሪያቤቱ ሠራተኞች በአዲስ አባባ አለርት ሆስፒታል ውስጥ፣ በአዳማ አዳማ ጀነራል ሆስፒታል ውስጥ እንዲሁም በአር ባምንጭ ሆስፒታል ችግኞችን መትከላቸው የሚታወስ ነው፡፡
በቀጣይም ሠራተኛውና አመራሩ የተተከሉትን ችግኞች መንከባከብና ተጨማሪ ችግኞችን ለመትከል ቃል መግባታቸው አስታውቀዋል፡፡