ማንኛዉም የምግብ ምርት በባለስልጣኑ ሳይመዘገብ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የተከለከለ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ማንኛዉም የምግብ ምርት በባለስልጣኑ ሳይመዘገብ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የተከለከለ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ማንኛውም የምግብ ምርት በባለስልጣኑ ሳይመዘገብ እና የገበያ ፊቃድ ሳያገኝ ለሽያጭ ማቅረብ፣ ማስተዋወቅ ወይም የምርት ይዘት፣ ዓይነትና ሂደት ለውጥ ማድረግ እንደማይቻል አስታወቀ፡፡ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በፀደቀው የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 71/2/ መሠረት የምግብ ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 42/2011…