ይህ መዘርዝር የኢትዮጵያ መሰረታዊ መድኃኒት መዘርዝር/Ethiopian National Essential Medicine List/ ሲሆን ለ7ኛ ጊዜ ተሻሽሎ የቀረበ ነዉ፡፡ መዘርዝሩን ለማሻሻል ቴክኒካል የስራ ቡድንና ኮር ቲም ተቋቁሞ የሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታዋች በመዳሰስ እንዲሁም ልዩ ልዩ ማጣቀሻወችን በመጠቀም የመጀመርያ ድራፍት ተዘጋጅቶ በሚመለከታቸዉ ልዩ ልዩ የባለድረሻ አካላት ምክክርና ዉይይት ከተደረገበት በኃላ የተሰጡ አስተያየቶችን በማካተት መዘርዝሩ እንዲዘጋጅ ተደርጋል፡፡ በመሆኑም ይህን መዘርዝር የበለጠ ለማዳበር ስለተፈለገ በድረገፅ የተጫነ ሲሆን ከተጫነበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት አስተያየታችሁን መስጠት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ማንኘዉንም አስተያየት በኢሜል heshete@efda.gov.et በሚለዉ አድራሻ መላክ እንደምትችሉ ማሳወቅ እንወዳልን፡፡