ይህ የዜጎች ቻርተር ሰነድ ባለስልጣን መስሪያቤታችን በአዋጅ ቁጥር 661/2002 በተሰጠው
ስልጣንና ተግባር መሰረት ለተገልጋዮቻችንና ለህብረተሰቡ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ዝርዝር፣
የአገልግሎት መስጫ ቦታዎች፣ አገልግሎቱ ለመስጠት ተገልጋዮቻችን ማJላት ያለባቸው
መስፈርቶችና
አገልግሎቱ ለመስጠት የሚፈጀው ጊዜ እንዲሁምበገባነው ቃል መሰረት
ለተገልጋዮቻችንአገልግሎቱ ሳንሰጥ ስንቀር ወይም በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደታችን ማንኛውም
ዓይነት ቅሬታ ሲኖራቸው ቅሬታ የሚያቀርቡበትና የግብረ መልስ አሰጣጥ ስርዓታችን እና
ሌሎች ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች የያዘ ማንዋል ነው፡፡ ይህም የመስሪያቤታችን አሰራር
ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ለማስኬድና መልካም አስተዳደር ከማስፈን አንፃር ጉልህ
ሚና ይጫወታል ብለን እናምለን፡፡
በዚህ መሰረት ማንዋሉ ለአጠቃቀም ቀላል እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን በበለጠ ግልፅነት
ለመፍጠር የሚከተሉት መረጃዎች ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡
–
–
–
ተገልጋዮች ለእያንዳንዱ አገልግሎት ለመጠየቅ መሙላት ያለባቸው የማመልከቻ ቅፆች
በሰነዱ መጨረሻ ላይ ተያይዘዋል፡፡ ስለሆነም ተገልጋዮች ለሚፈልጉት አገልግሎት
ለመጠየቅ የማመልከቻ ቅፁ በሞሙላትና
ሌሎች መስፈርቶች በማያያዝ ማቅረብ
ይኖርባችዋል፡፡
ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት ማማላት ያለባቸው መስፈርቶች በአገልግሎቱ መጨረሻ
ኮለመን የተጠቀሱ እንደተጠበቀ ሁኖ በእያንዳንዱ የቁጥጥር መመርያዎች በጥልቀት
በማንበብ በመመርያው ላይ የተጠቀሱ ተጨማሪ መስፈርቶች ማማላት ይኖርባችዋል፡፡
መመርያዎቹም ከባለስልጣን መስሪያቤቱ ድህረ ገፅ ማግኘት ይቻላል፡፡
ለእያንዳንዱ አገልግሎት ለማግኘት የሚከፈለው የአገልግሎት ክፍያ በዝርዝር የተጠቀሱ
እንደተጠበቁ ሁኖው በሚንስትሮች ምክርቤት ደንብ ቁጥር 370/2008 ላይ
የምግብ፣መድሀኒት፣ የጤና ተkማትና የጤና ባለሙያዎች ምዝገበና ፈቃድ አሰጣጥ
አገልግሎት ክፍያ ተመንን ለመወሰን የወጣ ደንብ በጥልቀት ማየት ያስፈልጋል፡፡
ተገልጋዮች በተጠቀሰው ጊዜ ገደብና የጥራት ደረጃ አገልግሎት ለማግኘት ማJላት ያለባቸው
መስፈርቶች በሙሉ አJልተው መገኘት ይኖርባችዋል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አገልግሎት
የሚሰጠው የስራ ክፍል በተቀመጠው የጊዜ ገደብ አገልግሎቱ ያልሰጠ እንደሆነ ተገልጋዮች
በተቀመጠው የቅሬታ አቀራረብ ስርዓት መሰረት ቅሬታቸው በየደረጃው ላለው አካል ማቅረብ