የኮረና ቫይረስ በሽታ አምጪ ተሕዋስያን በዓይን የማይታዩ በጣም ረቂቅ ስለሆኑ በቤት ውስጥ ከጨርቅ የሚዘጋጁ የፊት ጭንብሎች በበሽታው ከተያዘ ሰው የሚወጡ በቫይረሱ የተበከሉ የእርጥበት ቅንጣቶችን መከላከል እንደማያስችሉ የተለያዩ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሀገራት እነዚህን ከጨርቅ የተሠሩ የፊት ጭንብሎች በማህበረሰቡ ቢደረጉ የበሽታውን ሥርጭት ለመቀነስ ስለሚረዳ ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች ጭንብል ቢጠቀሙ ቫይረሱ እያለባቸው የሕመም ምልክት ካልታየባቸው ወደ ጤናኛ የቫይረሱን መተላለፍ ሊቀንስ እንደሚችል ይጠቁማል፡፡ የሀገራችን የጤና ሚኒስቴርም ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች የፊት መሸፈኛ ጭንብል እንዲጠቀሙ እየመከረ ይገኛል፡፡